ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላት ግንኙነት እየዳበረ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ተናገሩ |
![]() |
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 6 2003 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላት የግንኙነት መስክ እየዳበረ ወደ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገሩን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ተናገሩ።የኢትዮጵያ የቻይና ድፕሎማሲያዊ ግንኙነት አራት አሰርት አመታትን አስቋጥሯል።ያኔ ቻይናም የዛሬዋን ገጽታዋን ኢትዮጵያም አሁን ያለችብት ሁኔታ ላይ አልነበረችም።የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እየዳበረ መቶ አሁን ለደረሰበት ደረጃ ያበቃቸው ግን ከአስር አመት በፊት የነበራቸው ያልተገደበ የኢኮኖሚ ትብበር ማሳየታቸው እንደሆነ ይነገራል።በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ያፋሰሱ የቤጂንግ ባለሀብቶች 126 የደረሱ ሲሆን የካፒታል መጠናቸውም ከ400 ሚሊየን ዶላር በላይ መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ።የንግድ ልውውጥ መጠኑ ማደጉ የመሰረተ ልማት ዝርጋታና የድጋፍ ስምምነቶች መበራከታቸውም ቀጥሏል።ባለፉት ጥቂት አመታት ብቻ ኢትዮጵያን የሚጎበኝ የቻይና ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲሁም ወደ ቤጂንግ የሚያቀኑ የኢትዮጵያ መሪዎች ይበልጡኑ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱን የጠበቀ አደርጎታል።ለስራ ጉብኝት ቤጂንግ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፕሬዝዳንት ሁ ጂን ታዎን ጨምሮ ከሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በሁለቱ አገሮች የጋራ የኢኮኖሚ ትብብር ላይ ተወያይተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ባለፉት ዓመታት ቻይና ለኢትዮጵያ ያላትን አጋርነት አንስተዋል። |
Saturday, August 13, 2011
ኢትዮጵያ ከቻይና
http://www.fanabc.com/Story.aspx?L=wmedia/TiguashNekashWednesdayAugust102011.wma&ID=17202